የአሪዞና ፒማ ሕንዶች፣ የሰዎችና የእንስሳት ሁሉ አባት ቢራቢሮ እንደሆነ ይናገራሉ፤ እርሱም ቸርዊት ማኬ (የምድር ፈጣሪ) ነው። ክንፉን እያርገበገበ ከደመናት ወደ ሰማያዊ ገደሎች[…] ወረደ፤ ከገዛ ላቡም ሰዎችን ፈጠረ። ሰዎች እየተባዙ ሲሄዱ ራስ ወዳዶችና ተጨቃጫቂዎች ሆኑ፤ ቸርዊት ማኬም በገዛ እጁ ሥራ ተጸይፎ ሁሉንም በውኃ ሊያሰጥማቸው ወሰነ።[…]
ሃውክ የሚባል አንድ የተራሮች ሰይጣን ነበር፤ ሴት ልጆቻቸውን እየሰረቀ ወንዶች ልጆቻቸውንም ይገድል ነበር። […] ሱሃ በዝምታ ተከትሎት ወደ ሱፐርስቲሽን ተራሮች ገባ፤ ልጁ ልታቀርብለት የነበረውን የቁልቋል ወይን አደንዛዥ መድኃኒት ጨመረበት፤ ሰይጣኑ ጠጥቶ ሲደነዝዝ ሱሃ ከተደበቀበት ወጥቶ የደነዘዘውን ጭራቅ አንጎሉ እስኪፈስ ድረስ ቀጠቀጠው። […]
ፒማዎች በዚህ ትንቢት ጽኑ እምነት ስላላቸው የሱፐርስቲሽን ተራሮችን አያቋርጡም፤ ምክንያቱም ቸርዊት ማኬ እዚያ ተቀምጦ የክፋታቸው ጫፍ እስኪደርስ እየጠበቀ ነው፤ ያን ጊዜ ከተራራው ሰንሰለት ጀርባ ተገድቦ የቆመውን ታላቅ ባሕር በምድር ላይ ይለቀዋል።