የአሪዞና ፒማ ሕንዶች እንደሚሉት የሰውና የእንስሳት ሁሉ አባት ቢራቢሮው ቸርዊት ሜክ (መሬት-ሠሪ) ነበር፤ እርሱም ከደመናት ወደ ሰማያዊው ገደል እየበረረ ወርዶ[...] ከራሱ ወዝ ሰዎችን ፈጠረ። ሕዝቡ እየበዙ ሲሄዱ፣ ስግብግብና ጠበኞች ሆኑ፤ ስለዚህ ቸርዊት ሜክ በሠራው ሥራ ተስፋ ቆረጠ (ተጸየፈ)፣ ሁላቸውንም ለማስጠምም ወሰነ።[...]
የሴቶቻቸውን ልጆች የሚሰርቅና ወንዶች ልጆቻቸውን የሚገድል ሀውክ የተባለ ተራራማ አጋንንት ነበረ። [...] እርሱም በጸጥታ ተከተሎት ወደ ሱፐርስቲሽን ተራሮች ገባ፤ ሴት ልጁ ሊታደለው ያዘጋጀችውን የቁልቋል ወይን አደንዛዥ ዕፅ ጨመረበት፤ ከዚያም ከጠጣው በኋላ፣ ሱሃ ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ የተደነዘዘውን እኩይ መንፈስ ጭንቅላቱን መትቶ ደመሰሰው።[...]
ፒማዎች በዚህ ትንቢት በጣም ከመተመናቸው የተነሳ የሱፐርስቲሽን ተራሮችን አያቋርጡም፤ ምክንያቱም ቸርዊት ሜክ እዚያ ተቀምጦ ይገኛል — ከተራራው በስተጀርባ የተገደበውን ታላቅ ባህር በምድር ላይ ለመልቀቅ የሰዎች ክፋት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚደርስበትን ጊዜ ይጠብቃል።