የአሪዞናዎቹ የፒማ ሕንዶች እንደሚተርኩት ከሆነ፣ የሰው ልጆችና የእንስሳት ሁሉ አባት ከደመናት መካከል በክንፉ እየተንሳፈፈ ወደ ሰማያዊዎቹ ገደሎች የወረደውና ከገዛ ላቡ ሰውን የፈጠረው ቸርዊት ሜክ (ምድር ፈጣሪ) የተባለው ቢራቢሮ ነበር።[...] ሰዎቹም እየበዙ በሄዱ ቁጥር ራስ ወዳድና ጠበኛ ስለሆኑ፣ ቸርዊት ሜክ በገዛ የእጁ ሥራ ተጸይፎ ሁሉንም በውኃ ሊያሰጥማቸው ወሰነ።[...]
ሴት ልጆቻቸውን የሚነጥቅና ወንድ ልጆቻቸውን የሚፈጅ ሃውክ የተባለ አንድ የተራራ ጋኔን ነበር። [...] ሱሃም ድምፁን አጥፍቶ ተከትሎት ወደ ሱፐርስቲሽን ተራሮች ገባ፤ ሴት ልጁ ልታቀርብለት የነበረውንም የቁልቋል ወይን ጠጅ አደንዛዥ ዕፅ ቀላቀለበት፤ ጋኔኑም ወይኑን ጠጥቶ በደነዘዘ ጊዜ፣ ሱሃ ከተደበቀበት ወጥቶ የዛን እርኩስ ፍጡር አናት ፈረካከሰው። [...]
የፒማ ሕዝቦች በዚህ ትንቢት ላይ ያላቸው እምነት እጅግ የጸና ከመሆኑ የተነሳ የሱፐርስቲሽን ተራሮችን ፈጽሞ አያቋርጡም፤ ምክንያቱም በዚያ ቸርዊት ሜክ ከተራራው ሰንሰለት ጀርባ ተገድቦ የተኛውን ታላቅ ባሕር በምድር ላይ ለመልቀቅ የክፋታቸውን ጥግ እየተጠባበቀ ተቀምጧልና።